ኬርኤፕለፕሲ ኢትዮጵያ የሚጥል ህመም በአገራችን እያደረሰ ያለውንማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግር ስፋትና ጥልቀት በመመልከት በህመሙ የሚሰቃዩ ኢትዮጵያውያን የጤና ሁኔታእንዲሻሻል፤ የሚጥል ህመምን ማከም የሚችል የባለሙያዎች ቁጥር በጤና ተቋማት ላይ እንዲጨምር ስልጠናመስጠት፣ የህክምና እድሎችን ማመቻቸት፣ ስለህመሙ በህብረተሰቡ ውስጥ ያለው አስተሳሰብና አመለካከትእንዲቀየር ግንዛቤ መፍጠር እንዲሁም ህመሙ እንዳይከሰት የመከላከል ስራ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡
ራዕያችን
ኬርኤፕለፕሲ ኢትዮጵያ የሚጥል ህመም ያለባቸው ሰዎች ጤናማ፣ አምራች፣ ከመገለልና መድሎ ነፃ ሆነው ማየት የሚል ራዕይ ይዞ ይሰራል፡፡
ለበለጠ መረጃ የተያያዘውን መጽሔት ያንብቡ::