የሚጥል ህመም በማንኛውም ሰው እና የእድሜ ክልል ሊፈጠር የሚችል የአንጎል ነርቭ ህመም ሲሆን የረዥም ጊዜ ህክምና እንዲሁም በአኗኗር ላይ ለውጥ፤ ከፍ ያለ ክትትል እና እንክብካቤ የሚፈልግ ነው፡፡ ሀኪም በቃ እስካላለ ድረስ መድሀኒቱን ባለማቋረጥ በአግባቡ በመውሰድ፣ በቂ እንቅልፍ በመተኛት፣ አልኮሆል መጠጦችን እና አደንዛዥ እጾችን ባለመጠቀም መቆጣጠር ይቻላል፡፡