Advocacy in Partnership | CareEpilepsy Ethiopia

Through our policy advocacy program, we collaborate and coordinate with the Ministry of Health and other stakeholders to influence national policies; organizational practices and improve service provisions available for people living with epilepsy. 

We advocate for people with epilepsy to influence government policy and organisational practice so that people with epilepsy can get support to live a productive life.

Our advocacy work is participatory and encourages:-

  1. Patient representatives to be a voice for their challenges.
  2. The ministry of health to give focus on epilepsy, develop and fund the service.
  3. The Association of Ethiopia Neurologists to run joint projects.
  4. Enage otehr private, government, community associations, and charity organizations to work with us. 
  5. Community leaders, traditional healers to join our community conversation to support people with epilepsy.
  6. Partnership with international organizations to support our work.

So far, we have managed to run joint programmes in partnership with Ethiopia Neurologist Association, Addis Ababa sub-cities to expand our services in Addis Ababa, the Ministry of Health, and Region Health Bureaus through initiation and implementation of joint projects of clinical care and awareness-raising programmes.


ለታማሚዎች መብት መሟገት እና ድርጅታዊ ግንኙነቶችን ማዳበር

ኬርኤፕለፕሲ ኢትዮጵያ የሚጥል ህመም ታማሚዎች ላይ በሚደርሰው ማንኛውም ጉዳት ዙሪያ ድምፃቸው እንዲሰማና ሰብዓዊ መብታቸው እንዲከበር ከህብረተሰቡ አባላት ጋር በመሆን ትክክለኛ መሠረት ያደረገ አቀራረብን እና ድጋፍን ከፍ በማድረግ ጠንካራ ተሟጋችነቱን አሳይቷል፡፡

ድጋፍ ሰጭ ቡድን (የህሙማን ተወካዮችመመስረት

የችግሩ ባለቤት የሆኑትን የሚጥል ህመም ህሙማንና ቤተሰቦቻቸውን ተሳትፎ ለማጎልበት፣ ታማሚዎች በአገልግሎት ሰጭ ተቋማት በመድሃኒት አቅርቦትና በጤና ባለሞያዎች የሚገጥማቸዉን የአሰራር ችግሮች እንዲፈቱ ለመስራትና በሚጥል ህመም ላይ ያለውን ተፅዕኖ ለመቀየር እንዲሁም ቤት ለቤት በመንቀሳቀስ ምክክሮችንና ግንዛቤዎችን ለመስጠት ድርጅቱ ህሙማንና ቤተሰቦቻቸውን አሰባስቦ ትርጉም ያለው ተጨባጭ ለዉጥ ለማምጣት እንቅስቃሴ ማድረግ የሚችል፥ መርሃ ግብር የሚያሰናዳ ድጋፍ ሰጭ ቡድን (የህሙማን ተወካዮች ኮሚቴ) ጥቅምት 25/2010 እንዲቋቋም አድርጓል።

ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች ጋር መሥራት

በኢትዮጵያ በሚጥል ህመም ዙሪያ ላሉ ችግሮች መፍትሄዎቹ በጣም የተወሳሰቡና አንድ ድርጅት ብቻዉን ሊፈታው የማይቻል ነው፡፡ ስለሆነም ኬርኤፕለፕሲ ኢትዮጵያ ዘላቂ የልማት ግቦችን ለማሳካት፣ አዳዲስ ሀሳቦችን ለማመንጨት እና መፍትሄዎችን ለማምጣት ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች፣ ከሌሎች መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች፣ በበጎ አድራጎት አገልግሎት ላይ ከሚሳተፉ በጎ ፈቃደኞች እና ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ሁልጊዜም ግንኙነቱን አጠናክሮ በትብብር ይሠራል፡፡ ይህንንም የምናሳካበት ስትራተጂ፡-

  • ትኩረት ለሚጥል ህመም እንዲሰጥ እና ለህሙማኑ አስፈላጊው ድጋፍ እንዲደረግ ከህመሙ ተጠቂዎች እና ከህመምተኛዉ ቤተሰቦች ጋር በመተባበር፣
  • የሚጥል ህመም ህክምና እንዲስፋፋ፣ በበቂ ባለሙያዎች እንዲሰጥና የመድሀኒት አቅርቦት ችግር እንዲቀረፍ ከፌዴራል ጤና ሚኒስቴር፣ ከአዲስ አበባ ጤና ቢሮ፣ ከክፍለ ከተማና ወረዳ ጤና ጽ/ቤቶች፣ ከሆስፒታሎች፣ ከክልል ጤና ቢሮ፣ በዞን እና በወረዳ ደረጃ ከሚገኙ ጤና ተቋማት ጋር ሰፊ ግንኙነት በመፍጠር እና በጋራ በመስራት፣
  • በሚጥል ህመም ላይ ያለዉ የተሳሳተ አመለካከት እንዲለወጥ የቅስቀሳ ስራዎች፣ ስልጠናና ትምህርት ለተለያዩ አጋር ድርጅቶች ለምሳሌ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች፣ የማህበረሰብ አቀፍ ተቋማት፣ የኢትዮጵያ የነርቭ ሐኪሞች ማህበር፣ የመገናኛ ብዙሃን፣ ዩኒቨርሲቲዎች፣ የግል ድርጅቶች፣ ቤተ እምነቶች፣ መገናኛ ብዙሀን እና ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በመስጠት ነው፡፡