Our program aim to improve the physical and psychological wellbeing of people with epilepsy through medication, psychological, economic and transportation support to make them self-confident, gain self-worth and become self-sufficient.
CareEpilepsy Ethiopia offers:-
- Education to patients to manage epilepsy and coexisting conditions.
- Confidential and personal advice through our "Telephone Helpline Service" to people affected by epilepsy.
- Facilitate peer support group meetings.
- Home visit
- Emotional support (counselling) and action plan support (coaching) to patients and their families.
- Facilitate increased skill training to empower people with epilepsy to be self-sufficient through craft training.
የሚጥል ህመም ያለባቸውን ሰዎች ሙሉ ጤንነት እና ደህንነት ማሻሻል
የሚጥል ህመም ያለባቸው ሰዎች እና ቤተሰቦቻቸው ከህክምና አገልግሎቶች ባሻገር ብዙ የተለያዩ የማኅበረሰብ አገልግሎቶች እና የኢኮኖሚ ድጋፍ ይፈልጋሉ፡፡ ይህንንም ለሟሟላት የሕመምተኞችን የኑሮ ሁኔታና አጠቃላይ ደህንነት ለማሻሻል ድርጅታችን የሚከተሉትን ፕሮግራሞች ያከናዉናል፡፡
ለታማሚ ቤተሰብ የምግብ እና የቁሳቁስ ድጋፍ ማድረግ
- ድርጅታችን የህክምና እድሎችን ከማመቻቸት ባሻገር አቅም ለሌላቸው ታማሚዎችና ቤተሰቦቻቸዉ የምግብ እና የቁሳቁስ ድጋፍ ያደርጋል፡፡
ማህበራዊ ትስስርን ማጠናከር
- ታማሚዎች እንዲሁም ቤተሰቦቻቸው በየጊዜው እየተገናኙ በሚያጋጥማቸው የግልና የጋራ ጉዳዮቻቸው ላይ እንዲወያዩ እና የጋር ችግሮችን እንዲቀርፉ መድረክ በመፍጠር በተጨማሪም የአቻ ላቻ ግኑኝነትን በማጠናከር እንዲደጋገፉ ማስቻል፡፡ ለምሳሌ፡- ወርሀዊ አቻላቻ ስብሰባ፣ ኑ ቡና ጠጡ
የስነልቦና ማማከር አገልግሎት
- ታማሚዎች የሚደርስባችውን ማህበራዊ ተጽዕኖ (ችግሮች) መፍታት እንዲችሉ እና እንደማንኛውም ሰው መስራት እና ማድረግ የሚፈልጉትን ነገር መከወን እንዲችሉ የሚያግዛቸውን የስነ-ልቦና ድጋፍ መስጠት፡፡
ለታካሚዎች በአካልና በስልክ የምክርና መረጃ አገልግሎት መስጠት
- ለታካሚዎች በስልክ የምክርና መረጃ አገልግሎት መስጠት በአነስተኛ የኑሮ ደረጃ የሚኖሩ የሚጥል ህመም ታማሚዎችና ቤተሰቦቻቸው ያለባቸውን ኢኮኖሚያዊ ችግሮች መፍታት እንዲችሉ የሚያግዛቸው የሙያ ስልጠና መስጠት፡፡