We ran initiatives that raised awareness of epilepsy for the communicty. We use various tools to continue to educate the public:-
ስለ የሚጥል በሽታ ግንዛቤ መፍጠር
የሚጥል ህመም ህክምና የታማሚውን ቤተሰብና የህብረተሰቡን ድጋፍ ይጠይቃል፡፡ ይህ ድጋፍ በተገቢው ሁኔታ ሊተገበር የሚችለዉ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ስለህመሙ ያለው የተሳሳተ አመለካከትና ግንዛቤ ሲለወጥ፣ ህሙማን በወቅቱ ወደ ጤና ድርጅቶች ሄደው ህክምና ሲያገኙና በህመሙ ምክንያት የሚከሰተው የአካል ጉዳት መቀነስ ሲቻል ነው፡፡ ስለሆነም ይህን በሕብረተሰባችን ዘንድ ስለህመሙ የሚስተዋለውን የግንዛቤ ክፍተት መቀነስ እንዲቻል ድርጅታችን ለታማሚዎች፣ በጤና ማዕከሎች፣ በሆስፒታሎች እና በትምህርት ቤቶች እንዲሁም በማህበረሰብ መድረኮች ላይ ለምሳሌ በእድሮች ላይ በመገኘት ስለሚጥል ህመም ያስተምራል፡፡ በተጨማሪም ሰፋፊ የንቅናቄ ዘመቻዎች እንደ የሚጥል ህመም ሳምንት ፕሮግራም ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የሚሳተፍበት፣ የመገናኛ ብዙሀንን እንደ መሣሪያ በመጠቀም ትምህርት የሚሰጥበት፣ በሚጥል ህመም የሚወድቅ ሰው እንዴት መርዳት እንደሚቻል የሚያሳይ ትዕይንት በወጣቶች የሚቀርብበት፣ የግንዛቤ ማስጨበጫ የእግር ጉዞ የሚደረግበት እና የተለያዩ ዜማዎችንና መልዕክቶችን በማስተላለፍ ህብረተሰቡን የማነቃቃትና ግንዛቤ የመፍጠር ስራ ይሰራል፡፡