Wellbeing Support

Our program aims to improve the physical and psychological wellbeing of people with epilepsy through psychological and economic support to make them self-confident, gain self-worth and become self-sufficient.

CareEpilepsy Ethiopia Wellbeing Program Offers: 

1. Patient Education: We provide comprehensive education to patients, helping them manage epilepsy and coexisting conditions effectively.

2. Helpline Service: Our confidential advice service offers personalized support to individuals affected by epilepsy, addressing their concerns.

3. Peer Support Groups: We facilitate regular meetings for peer support, creating a supportive environment for sharing experiences and mutual encouragement.

4. Home Visits: We provide personalized support through home visits, catering to the specific needs of patients and their families.

5. Emotional and Action Plan Support: Our counseling services offer emotional support, while coaching sessions help develop action plans for overall well-being.

The CareEpilepsy Ethiopia Wellbeing Program is dedicated to providing education, support, and empowerment to individuals and families affected by epilepsy.



የሚጥል ህመም ያለባቸውን ሰዎች ሙሉ ጤንነት እና ደህንነት ማሻሻልየሚጥል ህመም  ያለባቸው ሰዎች እና ቤተሰቦቻቸው ከህክምና አገልግሎቶች ባሻገር ብዙ የተለያዩ የማኅበረሰብ አገልግሎቶች  እና የኢኮኖሚ ድጋፍ ይፈልጋሉ፡፡ ይህንንም ለሟሟላት የሕመምተኞችን የኑሮ ሁኔታና አጠቃላይ ደህንነት ለማሻሻል ድርጅታችን የሚከተሉትን ፕሮግራሞች ያከናዉናል፡፡ ለታማሚ ቤተሰብ የምግብ እና የቁሳቁስ ድጋፍ ማድረግ

  • ድርጅታችን የህክምና እድሎችን ከማመቻቸት ባሻገር አቅም ለሌላቸው ታማሚዎችና ቤተሰቦቻቸዉ የምግብ እና የቁሳቁስ ድጋፍ ያደርጋል፡፡

ማህበራዊ ትስስርን ማጠናከር

  • ታማሚዎች እንዲሁም ቤተሰቦቻቸው በየጊዜው እየተገናኙ በሚያጋጥማቸው የግልና የጋራ ጉዳዮቻቸው ላይ እንዲወያዩ እና የጋር ችግሮችን እንዲቀርፉ መድረክ በመፍጠር በተጨማሪም የአቻ ላቻ ግኑኝነትን በማጠናከር እንዲደጋገፉ ማስቻል፡፡ ለምሳሌ፡- ወርሀዊ አቻላቻ ስብሰባ፣  ኑ ቡና ጠጡ

የስነልቦና ማማከር አገልግሎት 

  • ታማሚዎች የሚደርስባችውን ማህበራዊ ተጽዕኖ (ችግሮች) መፍታት እንዲችሉ እና እንደማንኛውም ሰው መስራት እና ማድረግ የሚፈልጉትን ነገር መከወን እንዲችሉ የሚያግዛቸውን የስነ-ልቦና ድጋፍ መስጠት፡፡

ለታካሚዎች በአካልና በስልክ የምክርና መረጃ አገልግሎት መስጠት

  • ለታካሚዎች በስልክ የምክርና መረጃ አገልግሎት መስጠት በአነስተኛ የኑሮ ደረጃ የሚኖሩ የሚጥል ህመም ታማሚዎችና ቤተሰቦቻቸው ያለባቸውን ኢኮኖሚያዊ ችግሮች መፍታት እንዲችሉ የሚያግዛቸው የሙያ ስልጠና መስጠት፡፡