Community Education

Our public awareness is the pillar of our work to eradicate the stigma of epilepsy. Most people still believe that epilepsy is associated with evil spirit. That is why we bring awareness to the community and teach them that this is not something evil, but a very serious illness that can be treated with medication. We ran initiatives that raised awareness of epilepsy for the community.  We use various tools to continue to educate the public:-

  1. Offer training programs on epilepsy and Seizure First Aid.
  2. Distribute epilepsy teaching aid such as posters, leaflets, newsletters, videos to health centres, hospitals, and schools.
  3. Celebrate national and International and Epilepsy Day in partnership with other stakeholders. 
  4. Hold street campaigns in Addis Ababa.
  5. Conduct community epilepsy education .
  6. Run epilepsy education sessions at hospitals, health centers, schools, organizations and community groups. 

ስለ የሚጥል በሽታ ግንዛቤ መፍጠር 

የሚጥል ህመም ህክምና የታማሚውን ቤተሰብና የህብረተሰቡን ድጋፍ ይጠይቃል፡፡ ይህ ድጋፍ በተገቢው ሁኔታ ሊተገበር የሚችለዉ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ስለህመሙ ያለው የተሳሳተ አመለካከትና ግንዛቤ ሲለወጥ፣ ህሙማን በወቅቱ ወደ ጤና ድርጅቶች ሄደው ህክምና ሲያገኙና በህመሙ ምክንያት የሚከሰተው የአካል ጉዳት መቀነስ ሲቻል ነው፡፡  ስለሆነም ይህን በሕብረተሰባችን ዘንድ ስለህመሙ የሚስተዋለውን የግንዛቤ ክፍተት መቀነስ እንዲቻል ድርጅታችን ለታማሚዎች፣ በጤና ማዕከሎች፣  በሆስፒታሎች እና በትምህርት ቤቶች እንዲሁም በማህበረሰብ መድረኮች ላይ ለምሳሌ በእድሮች ላይ በመገኘት ስለሚጥል ህመም ያስተምራል፡፡ በተጨማሪም ሰፋፊ የንቅናቄ ዘመቻዎች እንደ የሚጥል ህመም ሳምንት ፕሮግራም  ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የሚሳተፍበት፣ የመገናኛ ብዙሀንን እንደ መሣሪያ በመጠቀም ትምህርት የሚሰጥበት፣ በሚጥል ህመም የሚወድቅ ሰው እንዴት መርዳት እንደሚቻል የሚያሳይ ትዕይንት በወጣቶች የሚቀርብበት፣ የግንዛቤ ማስጨበጫ የእግር ጉዞ የሚደረግበት እና የተለያዩ ዜማዎችንና መልዕክቶችን በማስተላለፍ ህብረተሰቡን የማነቃቃትና ግንዛቤ የመፍጠር ስራ ይሰራል፡፡